BunaTel እንዴት ይሠራል
ምዝገባ
የራስዎን የሞባይል ቁጥር ያስገባሉ፤ እኛ ኮድ በአጭር መልእክት እንልካለን። ኮዱን ሲጽፉ ይገባሉ፤ የይለፍ ቃል የለም። ለመጀመሪያ ጊዜ መተግበሪያው ስምዎንና የሚኖሩበትን አገር ይጠይቃል። ከኢትዮጵያ በስተቀር ከማንኛውም አገር መመዝገብ ይችላሉ፤ ምክንያቱም አገልግሎቱ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ለመደወል ነው።
የመጀመሪያ ደቂቃዎችዎ
አዲስ መለያ ወደ ኢትዮጵያ 5 ነፃ ደቂቃ ያገኛል፤ ለ3 ቀን ያገለግላሉ። ጥቅል ሲገዙ አይጠፉም።
ጥሪ ማድረግ
- እውቂያ ይምረጡ ወይም ቁጥር ይጻፉ።
- መተግበሪያው ጥሪው ከምን እንደሚከፈል ያሳያል፤ ከደቂቃዎችዎ፣ ወይም ከክሬዲትዎ እና የአንድ ደቂቃ ዋጋ።
- ስልክዎ በኢንተርኔት ከBunaTel ጋር ይገናኛል፤ BunaTel ደግሞ በተለመደው የስልክ መረብ የእነሱን ስልክ ይጠራል።
- እንደማንኛውም ጥሪ ያነሳሉ።
እርስዎ ዋይፋይ ወይም የሞባይል ዳታ ያስፈልግዎታል። እነሱ ምንም አያስፈልጋቸውም።
ጥሪ ምን ያስከፍላል
| የሆነው | የሚከፍሉት |
|---|---|
| አንስተው አውርታችኋል | ከተነሳበት እስከ ተዘጋበት ያሉትን ሰከንዶች |
| ጠርቶ ማንም አላነሳም፣ ወይም ተይዟል | ምንም |
| ተነስቶ በ5 ሰከንድ ውስጥ ተቋርጧል | ምንም |
| ድምፅ በአንድ አቅጣጫ ብቻ ተላልፏል (መረባችን እንዳየው) | ምንም |
| ጥሪውን ያበላሸ ሌላ ነገር | ከደረጃ መስጫው ገጽ ተመላሽ ይጠይቁ |
ደቂቃ፣ ጥቅል እና ክሬዲት
ጥቅል ማለት የማብቂያ ቀን ያላቸው ደቂቃዎች ናቸው፤ አንድ ጊዜ ይከፈልባቸዋል። ጥቅሎች ይደመራሉ፤ አዲሱ አሮጌውን አይተካም። ቀድመው የሚያበቁ ደቂቃዎች ቀድመው ጥቅም ላይ ይውላሉ።
ክሬዲት በአሜሪካ ዶላር ያለ ቀሪ ሂሳብ ነው። ለሚደውሉበት አገር ደቂቃ ከሌለዎት ጥሪውን ይከፍላል፤ ዋጋውን መተግበሪያው ከጥሪው በፊት ያሳያል።
በራሱ የሚታደስ ነገር የለም። መተግበሪያው ያለዎትንና እያንዳንዱ መቼ እንደሚያበቃ ይዘረዝራል።
አንድ መለያ፣ ብዙ ስልኮች
መለያዎ ስልክ ቁጥርዎ ነው። እስከ ሦስት ስልኮች ላይ መግባት ይችላሉ፤ ደቂቃዎችዎና ክሬዲትዎ መለያውን ይከተላሉ። መተግበሪያው የገቡባቸውን ስልኮች ይዘረዝራል፤ ማናቸውንም ማስወጣት ይችላሉ።
ከኢትዮጵያ ጥሪ መቀበል
በመተግበሪያው ውስጥ የሚጠራ የኢትዮጵያ የመልሶ መደወያ ቁጥር ለማቅረብ እየሠራን ነው። ገና አልተጀመረም። ሲጀመር ቁጥሩ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ መተግበሪያው ይናገራል፤ የተከፈለ ጥቅል እስካለዎት ድረስ፣ እና ከዚያ በኋላ ለ30 ቀን።
ግላዊነትዎ በአጭሩ
ጥሪዎች አይቀረጹም። እርስዎ ካልፈቀዱ በስተቀር እውቂያዎችዎ ከስልክዎ አይወጡም። ዝርዝሩ በግላዊነት ፖሊሲው (በእንግሊዝኛ) አለ።